የጤናማ አመጋገብ አስፈላጊነት

ለአጠቃላይ ጤንነት አመጋገብን ማስተካከል ለምን አስፈላጊ ሆነ?

አመጋገብን ማስተካከል ጤናችን አስፈላጊ የሆነበት ምክንያት የምንመገበው ምግብ በቀጥታ የሰውነታችን እድገት፣ተግባር እና በሽታ መከላከል ላይ ተጽእኖ ስላለው ነው።ዋና ዋና ምክንያቶች የሚከተሉት ናቸው።


1.የሀይል አቅርቦት(Energy Supply) ካርቦሃይድሬት፣ስቦች እና ፕሮቲኖች ለሰውነታችን እለታዊ እንቅስቃሴ የሚያስፈልገውን ሀይል ይሰጣሉ።ይህም
ከማሰብ ጀምሮ አካላዊ እንቅስቃሴ ያለውን ያጠቃልላል።


2. እድገት እና ጥገና(Growth and Repair)
ፕሮቲኖች፣ቫይታሚኖች እና ማእድናት ቲሹዎች(Tissue) ማለትም ጡንታዎችን፣ቆዳን እና አጥንቶችን ለመገንባት እና
ለመጠገን ይረዳል።


3. ጠንካራ በሽታን የመዋጋት አቅም(Strong Immunity)
የተስተካከለ የአመጋገብ ስርአት በሽታ የመከላከል አቅምን ያጠነክራል፣ሰውነታችን ኢንፌክሽኖች እና በሽታዎች እንዲዋጋ
ይረዳል።


4. ጤናማ የሰውነት ተግባራት (Healthy body Functions)
እንደ ቫይታሚን እና ማእድናት ያሉ ንጥረ ነገሮች የሰውነት አካላት ክፍሎችን(Organs)ሆርሞኖችን(Hormones)እና
የሰውነት የተግባር ስርዓቶችን(Systems) በአግባቡ እንዲሰሩ ያደርጋሉ። ምሳሌ የልብ ስርአት፣የአእምሮ ስርአት እና
የምግብ አፈጫጨት ስርአት


5. በሽታን መከላከል(Diseases Prevention)
የተመጣጠነ የአመጋገብ ስርአት ስር በሚሰዱ በሽታዎች የመያዝን አደጋ ይቀንሳል። ለምሳሌ ስኳር፣የልብ በሽታ፣ከመጠን
ያለፈ ውፍረት እና ደም ብዛት


6. የአእምሮ ጤንነት
ጥሩ የአመጋገብ ስርአት ለአእምሮ ጠንነት፣ለትኩረት(Concentration)፣ለጥሩ የአእምሮ ሁኔታ (Mood) እና ጭንቀትን
ለመቀነስ ይረዳል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *