ኩፍኝ
ኩፍኝ (Measles)
የኩፍኝ (ሚዝልስ) በሽታ በተለምዶ በተለያዩ ስሞች ይጠራል። ከእነሱም መካከል ወተቴ፣አንከሊስ እና አለሞቼ ይገኙበታል።የኩፍኝ በሽታ እጅጉን ተላላፊ በሽታ ነው። ይህ በሽታ ጸረ ኩፍኝ ክትባት ከመስፋፋቱ በፊት በየአመቱ ከ2 ሚሊዮን ያላነሱ ሰዎችን ለህልፈት ይዳርግ የነበረ አደገኛ በሽታ ነው። አሁንም ድረስ ክትባቱ ሙሉ በሙሉ ባልተስፋፋባቸው ሃገራት የኩፍኝ ወረርሽኝ ይከሰታል።
የኩፍኝ (ሚዝልስ) በሽታ ምልክቶች
- የኩፍኝ ቫይረስ ሰውነት ዉስጥ ከገባ በ10ኛው ቀን አከባቢ ትኩሳት እና የሰዉነት መዛል ይከሰታል
- የኩፍኝ ሽፍታ ከመታየቱ 2 ቀን ቀደም ብሎ አፍ ዉስጥ ቁስል መውጣት
- ራስ ምታት፣ የሆድ ህመም፣ተቅማጥ እናቁርጥማት ሊያስከትል ይችላል
- መላ ሰዉነትን ያካለለ ሽፍ’ታ
- ትኩሳት (>38.3°C)
- ሳል ወይም ንፍጥ ንፍጥ ማለት ወይም የአይን ልባስ መቅላት/ መቆጣት
