ሳይነስ
ሳይነስ በሽታ / sinusitis /
ሳይነስ (sinus) የሚባሉት በአፍንጫ ዙሪያ የሚገኙ በአየር የተሞሉ ክፍት ቦታዎች ናቸው። ሳይነሶች ከስራቸው ባለው የፊት አጥንት ስም ይጠራሉ(ለምሳሌ ማግዚላሪ (maxillary) ፣ ኢትሞይድ (ethmoid) እና ፍሮንታል(frontal) ይገኙበታል።እነዚህ
ሳይነሶች(sinuses) በርካታ ጥቅም አላቸው። የምንተነፍሰው አየር እርጥበታማ እና ሞቅ ያለ እንዲሆን ማድረግ፣ የድምጽ ቅላጼ እንዲያምር እና የፊት አደጋን ለመከላከል አስተዋጾ አላቸው። ተከታዩ ስእል የአፍንጫ ዙሪያ (paranasal sinuses) ሳይነሶችን
ያሳያል።
የሳይነስ ህመም ምልክቶች
የሳይነስ ህመም ምልክቶች የሚከተሉትን ሊያካትት ይችላል:
- በአፍንጫ ዙሪያ ያለ ህመም፤ ህመሙ ወደ ግንባር ወይም ጥርስ ድረስ ዘልቆ ሊሰማ ይችላል።
- ህመሙ በምናጎነብስበት፣በምናስነጥስበት ግዜ የመባባስ ባህሪ አለው።
- የአፍንጫ ፣ የጉንጭ ወይም የዐይን ሽፋኖች መቅላት ሊታይ ይችላል።
- የአፍንጫ ዙሪያ ፣የአይን ዙሪያ እና ግንባር ሲነካ የህመም ስሜት ሊኖር ይችላል።
- የአፍንጫ መደፈን ፤ የፊት ህመም እና የማሽተት አቅም መቀነስ ሌሎች የሳይነስ ህመም ምልክቶች ናቸው።
- ጉንፋን የታመመ ሰው ፣ የህመም ስሜቶቹ ከአንድ ሳምንት (7 -10) በላይ ከቆዩ ፣በተለይም ስሜቱ ከባድ ከሆነ እና ከፍተኛ የሰውነት ትኩሳት ፣ መግል የመሰለ የአፍንጫ ፍሳሽ ካለ ወይም የአይን ቆብ እብጠት (ኤቲሞይድ sinusitis) ካለ አጣዳፊ የሳይነስ ህመምን መጠርጠር እና ተገቢውን እርምጃ መውሰድ ያስፈልጋል። በተለይም ጉንፋኑ ማገገም ጀምሮ ሳለ ወዲያው የማገርሸት ምልክት ካሳየ የሳይነስህመም የመሆን እድሉ ሰፊ ነው።
