ቶንሲል

                    የቶንሲል በሽታ  (Pharyngitis/tonsillitis )

ይህንን ጉዳይ ለመግለጽ በማህበረሰቡም በጤና ባለሙያዎችም ዘንድ የተለያዩ ዘንድ በጣም የተለመዱ ቃላት ናቸው።በጤና ባለሙያዎች ዘንድ ደግሞ ቃላቶች ጥቅም ላይ ይውላሉ፡፡ ለምሳሌ እንጥል መውረድ እና ቶንሲል በማህበረሰቡ ቶንሲላይቲስ፣ፋሪንጃይቲስ ወይም ቶንሲሎፋሪንጃይቲስ የሚሉት ቃላት ይህንን በሽታ ለመግለጽ አገልግሎት ላይ ይውላሉ፡፡

በቫይረስ እና በባክቴሪያ የሚመጣ ቶንሲል በአብዛኛው ቀላል እና በራሱ ሊድን የሚችል ነው። ሆኖም የባክቴሪያ ቶንሲል በሽታ አሳሳቢ ጠንቆችን ሊያስከትል ይችላል። ከእነዚህም መካከል የልብ ቁስለት እና የኩላሊት መቆጣት ሁለቱ በጣም አሳሳቢ የሆኑ የባክቴሪያ ቶንሲል በሽታ ጠንቆች ናቸው፡፡

የቶንሲል በሽታ እንዴት ይተላለፋል ? የቶንሲል በሽታ የሚያስከትሉ ቫይረሶች እና ባክቴሪያዎች ተላላፊ ናቸው። መተላለፊያ መንገዳቸው ፡-

  1. ዕቃዎችን ፣ ምግብን ወይም መጠጥን ከታማሚ ጋር መጋራት
  2. ከታመመ ሰው ጋር የቅርብ ግንኙነት
  3. የተበከለ ነገርን መንካት እና ከዚያ አፍንጫዎን ወይም አፍዎን መንካት
  4. የታመመ ሰው በሚያስልበት ወይም በሚያስነጥስበት ጊዜ ወደ አየር የሚተላለፉ ጥቃቅን ቅንጣቶችን ወደ ውስጥ መሳብ

       የቶንሲል በሽታ ምልክቶች

ከላይ እንደጠቀስኩት የቶንሲል በሽታ በዋናነት በቫይረስ አማካኝነት የሚከሰት ነው:: እናም የተለየ ህክምና አያስፈልገውም። ስለሆነም የቫይረስ ቶንሲል በሽታን ከባክቴሪያ ቶንሲል በሽታ መለየት እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡ የቫይረስ ቶንሲል በሽታን ከባክቴሪያ በምልክቶቹ መለየት ይቻላል።

ዋናው የቶንሲል ምልክት የጉሮሮ ህመም እና ለመዋጥ መቸገር ነው።ሳል፣የአይን መቅላት፣ንፍጥ ንፍጥ ማለት የቫይረስ ቶንሲል በሽታን ሲያሳይ፤ በአንጻሩ ደግሞትኩሳት፣አንገት ላይ ፍርንትት ወይም ንፊፊት መውጣት፣ ሳል አለመኖር የባክቴሪያቶንሲል በሽታን ያሳያል።የባክቴሪያ ቶንሲል ህመም በድንገት የሚከሰት ሲሆን ትኩሳት፣ራስ ምታት እና የሳል አለመኖር ዋና ዋና ምልክቶቹ ናቸው።

     የቶንሲል በሽታ መከላከያ መንገዶች

  • ቶንሲል ከሰው ወደ ሰው የሚተላለፍ በመሆኑ አካላዊ ቅርርብን በማስወገድ ልንከላከለው እንችላለን።
  • የቶንሲል ህመም በስፋት የሚከሰተው ዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ፣አነስተኛ የንጽህና ደረጃ ያላቸው እና አንድ ላይ በብዛት (ብዙ ቤተሰብ፣ትምህርት ቤት) የሚኖሩ ሰዎች ላይ በመሆኑም የኑሮ ደረጃን ማሻሻል
  • የንጽህና ደረጃን ማዘመን
  • አፍንጫዎን ወይም አፍዎን ከመንካትዎ በፊት እጅዎን መታጠብ
  • ከታመመ ሰው ጋር ምግብ ፣ መጠጥ ወይም ዕቃ ከማጋራት መቆጠብ
  • የጥርስ ብሩሽዎን በመደበኛነት ይተኩ ይቀይ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *