ትራኮማ

       ትራኮማ (Trachoma)

ትራኮማ የዓለማችን ቀዳሚ ዓይነ ስውነትን የሚያስከትል ተላላፊ በሽታ ነው፡፡ ይህ በሽታ ክላሚዲያ ትራኮማቲስ (Chlamydia trachomatis) በተባለ ባክቴሪያ ምክንያት የሚመጣን ሥር የሰደደ የአይን ዉስጥ ቁጣ (keratoconjunctivitis)ያስከትላል።

ክላሚዲያ ትራኮማቲስ በበሽታው ከተያዘ ሰው ዓይኖች ወይም ከአፍንጫ ጋር ንክኪ ካለ ወይም ከተዘዋዋሪ ግንኙነት ጋር ፣ ለምሳሌ በበሽታው ከተያዘ ሰው አይን ወይም አፍንጫ ጋር ንክኪ ባላቸው ልብሶች ወይም ዝንቦች አማካኝነት ሊሰራጭ ይችላል። ዝቅተኛ የንፅህና አጠባበቅ ልምድ ፣ የተጨናነቀ (ብዙ ሰው አንድ ላይ እፍግ ብሎ መኖር) የኑሮ ሁኔታ እና በቂ ያልሆነ ንጹህ ውሃ እና መፀዳጃ ቤቶች አለመስፋፋት የትራኮማ መስፋፋትን ከፍ ሊያደርጉ ይችላሉ። በሽታው በዋነኝነት የሚከሰተው በልጆች እና በሚንከባከቧቸው እናቶች ላይ ነው። ትራኮማ የሚያስተላልፉ ዝንቦች እንቁላሎቻቸውን በተለየ ሁኔታ በሰው ሰገራ ላይ ይጥላሉ።በዚህም በሰው ሰገራ (መሬት ላይ የመጸዳዳት ዉጤት ነው) ላይ በመራባት ዝንቦች የትራኮማን በሽታ ከሰው ወደ ሰው ለማስተላለፍ እድሉን ያገኛሉ።

     የትራኮማ ምልክቶች

የትራኮማ በሽታ ሁለት አይነት ደረጃዎች አሉት፤አጣዳፊ (active trachoma) እና ጠባሳ የፈጠረ (scarring (cicatricial) ናቸው።የትራኮማ ምልክቶች ብዙውን ጊዜ በሁለቱም ዓይኖች ላይ ይስተዋላሉ እና የሚከተሉትን ሊያካትቱ ይችላሉ።

  1. መለስተኛ ማሳከክ እና የዓይን እና የዐይን ሽፋኖች ህመም
  2. የዓይን ማልቀስ እና ቅምጥ መያዝ እና የዓይን ማበጥ
  3.  የብርሃን መፍራት ወይም ማስጠላት
  4.  የዓይን ሕመም ወይም የዓይን መቅላት
  5. የእይታ መቀነስ

ሁሉም የትራኮማ ምልክቶች በላይኛው የአይን ክዳን ላይ ይብሳሉ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *