የኮሶ ትል በሽታ (Tapeworms)
የኮሶ ትሎች ሲስቶድስ( Cestodes) ይባላሉ፣ ከሌሎቹ የሆድ ትላትሎች ለየት የሚያደርጋቸው አንዱ ባህሪ ሰውነታቸው ክፍልፋይ (ሴግመንትድ ወርም)ያለው መሆኑ ነው ። ሁለት አይነት የኮሶ ትሎች የተለየ ትኩረት ይሻሉ። የከብት ( Taenia saginata ) እና የአሳማ (Taenia solium) ኮሶ ትሎች ዋነኞቹ የኮሶ ትሎችናቸው። ሌላኛው የሲስቶድ ትል በእኛ ሃገር በስፋትም ባይሆን በመጠኑ የሚከሰተው የትል አይነት የውሻ ኮሶ ወይም ኢክኖኮከስ ግራኑሎሲስ (echinococcosis)ነው።