የወባ በሽታ

የወባ በሽታ

የወባ በሽታ ገዳይ ከሆኑ የፕሮቶዘዋ በሽታዎች መካከል አንዱ ነው። የወባ በሽታ በተለከፈች (እንፌክተድ) ሴት የወባ ትንኝ (አኖፊለስ ሞስኪቶ) አማካኝነት ወደ ጤናማ ሰው የሚተላለፍ በሽታ ነው። የወባ በሽታ ትኩሳት ዋነኛው ምልክቱ ሲሆን በደም ምርመራ የበሽታውን መኖሩ ማረጋገጥ ይቻላል። የወባ በሽታን ለማከም የሚጠቅሙ የተለያዩ መድኃኒቶች አሉ። ሆኖም ተገቢዉን ሕክምና ካላገኘ ወባ ገዳይ ነው። የወባ በሽታን መከላከል ይቻላል።

የወባ መንስኤ እና መተላለፊያ መንገዶቹ

የወባ በሽታ ፕላዝሞድየም (plasmodium) በተሰኘ የፕሮቶዘዋ ዝርያ አማካኝነት ይከሰታል። አምስት አይነት የፕላዝሞድየም ዝርያዎች የወባ በሽታን በማምጣት ይታወቃሉ። እነሱም ፦

  1. ፕላዝሞድየም ፋልስፓረም (P.Falciparum)
  2. ፕላዝሞድየም ቫይቫክስ (P.Vivax)
  3. ፕላዝሞድየም ኦቫለ (P.Ovale)
  4. ፕላዝሞድየም ማላርዬ (P.malariae)
  5. ፕላዝሞድየም ኖውሌሲ(P.knowlesi) ናቸው፡፡

አብዛኛው በወባ ምክንያት የሚከሰተው ሞት በፕላዝሞድየም ፋልስፓረም አማካኝነት ነው ። ፕላዝሞድየም ኖውሌሲ እና አንዳንዴም ፕላዝሞድየም ቫይቫክስ የከፋ የወባ በሽታ ሊያስከትሉ ይችላሉ።

  • ወባ ወደ ሰው የሚተላለፈው ሴት የወባ ትንኝ ወይም ቢምቢ ደም በምትመጥበት ሰዓት ስፖሮዞይት (sporozoite) የሚባሉትን የፕላዝሞድየም ህዋሳት ወደሰዉየው አካል ከምራቅ እጢዎቿ ስትረጭ ወይም ስታስገባ ነው።

የወባ በሽታ ምልክቶች

የወባ በሽታ የተለያዩ ምልክቶች ያሉት ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ፡-

  • የሰዉነት ትኩሳት መጨመር
  • ትኩሳት ማለት የሰዉነት ሙቀት ከ5 ዲግሪ ሴንቲግሬድ በላይ መሆን
  • ብርድብርድ ማለት እና መንቀጥቀጥ
  • የምግብ ማስጠላት
  • ቁርጥማት
  • ራስ ምታት
  • አጠቃላይ የሆነ የጤነኝነት ስሜት ማጣት የተለመዱ የወባ በሽታ ምልክቶች ናቸው።
  • ራስን መሳት
  • አይን ቢጫ መሆን እና የሽንት መጠን ማነስ
  • የሰዉነት መድከም፣ መገርጣት እና ሌሎችም

የወባ በሽታ መከላከያ ዘዴዎች

  1. ቤትን በ ፀረ ወባ ትንኝ መድሃኒት መርጨት
  2. ወባን በቶሎ ማከም
  3. ወባማ ወደሆኑ አከባቢዎች አለመሄድ ወይም ወባማ አከባቢዎችን ለቆ ወባ የሌለበት ቦታ መኖር
  4. ኬሞፕሮፍላክሲስ (ወደ ወባማ ቦታዎች ለሚሄዱ ሰዎች አስቀድሞ የወባ መድሃኒት መውሰድ )
  5. ክትባት

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *