ጉንፋን

ጉንፋን (Commoncold)

የላይኛው የመተንፈሻ አካል ኢንፌክሽን ወይም ጉንፋን ብዙ ሰዎችን ወደ ጤና ተቋም እንዲሄዱ ከሚያደርጉ የጤና ችግሮች አንዱ ነው።ጉንፋን በአብዛኛው በቀላሉ እና በራሱ የሚያገግም አፍንጫን እና ጉሮሮን የሚያጠቃ ህመም ነው።ጉንፋን ምንም እንኳን ለሞት በመዳረግ የሚታወቅ በሽታ ባይሆንም ታማሚውን ከስራ እና ትምህርት የሚያስተጓጎል ህመም ነው፡፡

መንሳኤዎች

የጉንፋን አምጪ ቫይረሶች በዋናነት ከአፍንጫ በሚወጣ ፈሳሽ፣ በትንፋሽ ቅንጣቶች፣ በንክኪ፣ በፎጣዎች እና በሌሎች መንገዶች ከሰው ሰው ይተላለፋሉ።ቫይረሶቹ በዋናነት የሚተላለፉት ምልክት መታየት ከጀመረበት እስከ ሶስት ቀናት ድረስ ነው። የጉንፋን መተላለፊያ መንገዶችን በሁለት እንከፈለዋለን፤ እነሱም ቀጥታ ንክኪ (direct contact) እና ተዘዋዋሪ ንክኪ (indirect contact) ናቸው፡፡ ቀጥተኛ ንክኪ የሚባለው የጉንፋን አምጪ ቫይረሱ ከታማሚው በቀጥታ ወደ ሌ ሰው ሲገባ ነው (ለምሳሌ በማስነጠስ ግዜ)። በአንጻሩ ተዘዋዋሪ ንክኪ የሚባለው የጉንፋን አምጪ ቫይረሱ እቃ ላይ አርፎ ፣ የተበከለዉን እቃ ሌላ ሰውን በሚገለገልበት ግዜ ወይም በኋላ ቫይረሱ ወደ ሰዉነት (አፍንጫ ወይም አፍ) ሲገባነው።

የጉንፋን ምልክቶች

ጉንፋን ሲጀምር የአፍንጫ መድረቅ እና መደፈን (stuffiness) በአንድኛው ወይም በሁለቱም አፍንጫዎች ይስተዋላል።ወዲያው ንጹህ ዉሃማ ፈሳሽ ከአፍንጫ መውረድ ይጀምራል።በተጨማሪም የአይን እና የአፍንጫ መቅላት ይኖራል።የራስ ምታት፣ የምግብ ጣእም መቀነስ እና አጠቃላይ የሰውነት መዛል የጉንፋን ተጠቂ ሰው ላይ ሊታዩ ይችላሉ። አልፎ አልፎ ትኩሳት፣ የድምጽ መጎርነን እና የጉሮሮህመም ሊከሰት ይችላል።

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *