የአመጋገብ ስርአት አንድን የጤና እክል(በሽታ) እንዴት ይቀንሳል
አንዳንድ የጤና እክሎችን ለመከላከል/ለመቀነስ እንዲረዳን ማብዛት እና መቀነስ ያሉብን የምግብ አይነቶች እንደሚከተለው
ተዘርዝሯል።
1.
የስኳር በሽታ/ደም ብዛት
ማብዛት ፦ ጥራጥሬዎችን፣አትክልት፣ስስ ፕሮቲን(lean protiens)፣ከፍተኛ ፋይበር ያላቸው ምግቦችን(high fiber foods)
መቀነስ፦ ስኳራማ ምግቦች፣የተጣሩ ካርቦሃይድሬቶች(refined carbs)፣ጣፋጭ እና ለስላሳ መጠጦች
ጥቆማ፦ ጥቂት መመገብ፣ቋሚ በሆኑ ሰዓታት ተከታትሎ መመገብ የደም ግፊትን ለመቆጣጠር ይረዳል
2. የልብ በሽታ እና የደም ብዛት
ማብዛት ፦ፍራፍሬዎች ፣አትክልቶች፣ጥራጥሬዎች፣አሳ ፣ለውዝ፣የወይራ ዘይት(olive oil)
መቀነስ፦ ጨው ፣በዘይት የተጠበሱ ምግቦች፣ቀይ ስጋ፣በፋብሪካ የተቀነባበሩ ምግቦች
ጥቆማ፦ በዘይት ከተጠበሱ ምግቦች ይልቅ የተጋገሩ ወይም በእሳት የበሰሉ ምግቦችን መመገብ
3. ከመጠን ያለፈ ውፍረት
ማብዛት ፦ ምግቦች ላይ ትኩረት ማድረግ፣ አትክልት ፣ስስ ፕሮቲን(lean proteins) እና ጥራጥሬዎችን ማብዛት
መቀነስ፦ስኳራማ መጠጦች ፣ጤናማ ያልሆኑ ምግቦች(junk foods)፣መጠኑ የበዛ ምግብ
ጥቆማ፦ እንቅስቃሴ ማብዛት ፣ቀስ ብሎ መመገብ ከመጠን በላይ ላለመመገብ እንዲያግዘን
4. የደም ማነስ
ማብዛት ፦ በአይረን የበለጸጉ ምግቦችን መመገብ(ስጋ፣ስፒናች፣ባቄላ፣ምስር) እንዲሁም ቫይታሚን ሲ(ብርቱካን፣ቲማቲም)
መመገብ አይረኑን ወደ ሰውነታችን ለመሳብ ይረዳል
መቀነስ፦የበዛ ሻይ እና ቡና ሰውነታችን አይረንን እንዳይስብ ያግዳል
ጥቆማ፦አይረን ያላቸውን ምግቦች ቫይታሚን ሲ ከበለጸጉ ፍራፍሬዎች ጋር አጣምሮ መመገብ
5. የአጥንት እና መገጣጠሚያ ችግሮች(Osteoporosis Arthritis)
ማብዛት፦ በካልሲየም የበለጸጉ ምግቦች(ወተት፣እርጎ፣ቅጠላ ቅጠሎች(leaf greens) እና ቫይታሚን ዲ (የጸሀይ ብርሀን፣
እንቁላል እና አሳ
መቀነስ፦ የበዛ ጨው፣ለስላሳ መጠጦች
ጥቆማ፦ የክብደት ማንሳት ስፖርት መስራት ለአጥንት ጥንካሬ ይረዳል
6. የምግብ መፈጨት ችግሮች (የሆድ ድርቀት ፣የጨጓራ ቁስለት ወዘተ)
ለሆድ ድርቀት፦ ፋይበሮችን አብዝቶ መመገብ(ፍራፍሬዎች፣አትክልቶች፣ጥራጥሬዎች)እና ውሀ በብዛት መጠጣት
ለጨጓራ ቁስለት/አሲድ፦የተቀመመ አሲድ ያላቸውን ምግቦች አለመመገብ ሲመገቡ በአንድ ጊዜ መጠኑ አነስ ያለ ምግብን
መመገብ በቀን ውስጥ አነስተኛ መጠን ያለውን ምግብ ደጋግሞ በሰአታት ልዩነት መመገብ
ጥቆማ፦ ፕሮባዮቲኮች(እርጎ) ለአንጀት ጤንነት ይረዳል
ማጠቃለያ ፦ ጥሩ የአመጋገብ ስርአት ትክክለኛ ምግቦች ላይ እና የሚጎዱ ምግቦችን በመለየት ብዙ የጤና አክሎችን
ለመከላከል፣ለመቆጣጠር እና ለመቀነስ ይረዳሉ
