ጥሩ የሆነ አመጋገብን በየእለቱ ህይወታችን ውስጥ ለማካተት ተግባራዊ ጥቆማዎች
ጥሩ የሆነ አመጋገብን በየእለቱ ህይወታችን ውስጥ ለማካተት ተግባራዊ ጥቆማዎች ምንድን ነው?
ጥሩ የአመጋገብ ስርአትን እለታዊ ህይወታችን ላይ ለማካተት የሚረዱ ተግባራዊ ጥቆማዎች የሚከተሉት ናቸው።
1.የተለያዩ አይነት ምግቦችን መመገብ፦ፍራፍሬዎች፣አትክልቶች፣ጥራጥሬዎች፣ፕሮቲኖች እና ጤናማ ስቦችን በዕለታዊ
ምግባችን ማካተት
2. የምመገበውን ምግብ መጠን መቆጣጠር፦ የተመጠነ ምግብን በማቅረብ ከመጠን በላይ መመገብን ማስቀረት እና ሲጠግቡ
ማቆም
3. በቂ ውሃ መጠጣት ፦ቀኑን ሙሉ በቂ ውሃ መጠጣት ስኳራማ ከሆኑ ለስላሳ መጠጦች መራቅ
4. በፋብሪካ የተመረቱ ምርቶች(processed foods ) እና ጤናማ ያልሆኑ ምግቦችን(junk foods) መቀነስ ስኳራማ የሆኑ
የመክሰስ ምግቦችን (snacks)፣ ለስላሳ መጠጦችን እና ፈጣን ምግቦችን (fast foods) መቀነስ
5. ጤናማ የማብሰል መንገዶችን መጠቀም፦በዘይት ከመጥበስ ፋንታ በእሳት መጥበስ፣በእንፋሎት ማብሰል/መጋገር
6. የተመጣጠነ እለታዊ ምግብን እቅድ ማውጣት ፦ ቁርስ ፣ምሳ እና እራት ሁሉም ካርቦሃይድሬት፣ፕሮቲን እና የአትክልት
ቅይጥ እንዳለው ማረጋገጥ
7. በምግብ ሰአታት መካከል የምንመገባቸውን ቁርሳ ቁርስ ምግቦች(Snacks) በብልሀት መምረጥ ፦ በድንች ጥብስ(chips)
እና ጣፋጮች ፋንታ ለውዝ፣ፍራፍሬዎች እና እርጎን መምረጥ
8. ቁርስን አለማሳለፍ፦ ቀናችንን ጤናማ ምግብ በመመገብ መጀመር የሰውነታችንን ሀይል እና የአእምሮ ትኩረትን
ለመጨመር ይረዳል።
9. የታሸጉ ምግቦችን ጽሁፍ ማንበብ፦ በታሸጉ ምግቦች ላይ ያለው የኒውትሪሽን ዝርዝር በማንበብ የተደበቁ ስኳሮች፣ጨው
እና ጤናማ ያልሆኑ ስብ አለመኖሩን ማረጋገጥ
10. ማመጣጠንን መለማመድ፦ በጣፋጭ ምግቦች አለፍ አለፍ ብሎ መደሰት ነገር ግን መመጠን
በአጭሩ በብልሀት መመገብ፣ውሀ መጠጣት፣ጤናማ ያልሆኑ ምግቦችን መቀነስ እና የተመጣጠኑ የምግብ አይነቶችን መመገብ
