የአመጋገብ ስርዓት
የአመጋገብ ስርአት ምንድን ነው?
የአመጋገብ ስር አት ማለት ስለምግብ እና ሰውነታችን ምግብን እንዴት ለእድገት፣ለሀይል እና ጤንነትን ለመጠበቅ
እንደሚጠቀምበት የሚያጠና ሳይንስ ነው።
የኒውትሪሽን ሳይንስን ለመረዳት የሚከተሉትን መረዳት ያስፈልጋል።
Nutrients (ንጥረ ነገሮች)፦ ምግብ ውስጥ የሚገኙ ለሰውነታችን አስፈላጊ የሆኑ ንጥረ ነገሮች ምሳሌ፦ ካርቦሃይድሬትስ
(Carbohaydrates)፣ፕሮቲን(proteins)፣ስቦች(Fats)፣ቫይታሚኖች(Vitamins)፣ማእድኖች(Minerals እና ውሃ
Process (ሒደት) ፦አመጋገብ ሰውነታችን ምግብን የሚስብበት፣የሚፈጭበት፣የሚያጓጉዝበት እና የሚጠቀምበት
መንገድ
Balance (ምጣኔ) ፦ ጤነኛ ለመሆን እና በሽታን ለመከላከል ምን ያህል ምግብ እና ምን አይነት ምግብ መመገብ
እንዳለብን
