የሳንባ ምች
የሳምባ-ምች (ኒውሞኒያ-pneumonia)
የሳምባ-ምች ፤ ሳምባ በአይን በማይታዩ ተህዋሲያን ሲጠቁ የሚመጣ ችግር ነው፡፡በሶስት ይከፈላል፤ እነሱም ማህበረሰብ በቀል (community-acquired)፣ድረስ በምርመራ እና በህክምና ደረጃ ፈታኝ እንደሆነ ቀጥሏል።የሳምባ ምች የሳምባ-ምች ቀላል የማይባል ህመም እና ሞት የሚያመጣ ችግር ቢሆንም አሁን ሆስፒታል በቀል (hospitalacquired) እና ቬንቲሌተር (የመተንፈሻ አጋዥ መሳሪያ) (Ventilator-associated)የሳምባ ምች ናቸው። አሁን አሁን ብዙ መድሃኒት የተለመዱ የሳምባ-ምች አምጪ ባክቴሪያዎች እየተበራከቱ ነው።
የሳምባ-ምች ምልክቶች
የሳምባ ምች ምልክቶች የተለያዩ ናቸው፤ ከምልክቶቹ መካከል፣ ደም የቀላቀለ አክታ፣ ሳል፣ ትኩሳት እና ትንፋሽ ማጠር ይገኙበታል። አካለዊ ምርመራ ላይ ተጨማሪ ድምጾች (rales) በስቴቴስኮፕ (stethoscope) ይሰማሉ፣ የሰዉነት ኦክስጂን መጠን (hypoxemia) ማነስ ሊሰተዋል ይችላል።
ለሳምባ ምች የሚያጋልጡ ብዙ ነገሮች አሉ። ከእነዚህም ዉሰጥ የተወሰኑት፦
- አልኮል መጠጣት
- የሚጥል በሽታ
- ዘውታሪ (chronic) የሳምባ በሽታ (አስም፣ )
- የሰውነት በሽታ መከላከል አቅም መዳከም (ኤች አይ ቪ)
- ስኳር በሸታ
- ደም ካንሰር (ካንሰር)
- የእድሜ መግፋት ( 70 አመት)
- ሲጋራ ማጨስ
- የልብ ድካም እና የኩላሊት ድካም
- ሆቴል ዉስጥ መቆየት (Legionella)
