የሳንባ ነቀርሳ

ቲቢ (Tuberculosis)

የቲቪ በሽታ ማንኛውንም ሰው ሊያጠቃ ይችላል። ሆኖም የኤች አይ ቪ ህሙማንን በተለየ ሁኔታ ያጠቃል። በአለም አቀፍ ደረጃ ሲሶ ያህሉ የኤድስ ሞት ከቲቢ በሽታ ጋር የተያያዘ ነው። እንዲሁም የቲቢ በሽታ ከ10 እስከ 15 በመቶ ለሚሆነው የኤች አይ ቪ ሞት ግምባር ቀደም ምከንያት ነው። የኤች አይ ቪ ህሙማን በቲቢ የመጠቃት እድላቸው ኤች አይ ቪ ከሌለበት ሰው አንጻር በመቶ እጥፍ ይበልጣል።የቲቢ በሽታ በስፋት የ25 እስከ 44 አመት እድሜ ክልል ዉስጥ ያሉ ሰዎችን ያጠቃል።

የቲቢ በሽታ  ምልክቶች

የቲቢ በሽታ የተለያዩ ምልክቶችን ያሳያል፤ ምልክቶቹ እንደ ሲዲ ፎር ልኬቱ ይለያያሉ። በአንጻራዊነት ከፍ ያለ ሲዲ ፎር ቁጥር ያላቸው ሰዎች ላይ የቲቢ በሽታ ሲከሰት አይነተኛ ምልክቶችን ያሳያል።

  • የሲዲ ፎር ቁጥራቸው አናሳ የሆነባቸው ሰዎች ላይ ሲከሰት ያልተለመዱ የሆኑ ምልክቶችን ሊያሳይ ይችላል።
  • የሳምባ ቲቢ ፦ የሳምባ ቲቢ ምልክቶች
  • ሳል
  • አክታ
  • ትኩሳት
  • የሰዉነት መቀነስ (መክሳት)
  • የሌሊት ላብ እና የራጅ ምርመራ ላይ የላይኛው የሳምባ ክፍል መጎዳት ያካትታል።
  • ዝቅተኛ የሲዲ ፎር ቁጥር ያላቸው የኤች አይ ቪ ህሙማን ላይ የራጅ ምርመራው
  • የታችኛው ሳምባ ክፍል መጠቃት
  • የፈሳሽ መቋጠር
  • የፍርንትት (hilar and/or mediastinal adenopathy) መኖር እና ሌሎች ያልተለመዱ የራጅ ምልክቶች ሊታዩባቸው ይችላል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *