ታይፈስ

ታይፈስ

ታይፈስ ምንድን ነው ?

ታይፈስ አጣዳፊ የትኩሳት አምጪ ህመም (acute febrile illness) ነው።ሪኬትሲያ ((rickettsia or orienta bacteria) የተባሉ ባክቴርያዎች የታይፈስ መንስኤ ናቸው። የግል እና የአከባቢ ንጽህና መዘመን ታይፈስን ከበለጸጉት ሃገራት ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ አጥፍቶታል። በአንጻሩ የንጽህና ችግር ያለባቸው አከባቢዎች ታይፈስ አሁንም አንዱ የጤና እክል እንደሆነ ቀጥሏል።

የታይፈስ መንስኤን

ሪኬትሲያ የተባሉት ግራም ኔጌቲቭ ኮኮባሰላይ ባክቴሪያ የታይፈስ አምጪ ተህዋሲያን ናቸው።ይህ ባክቴሪያ የተለያዩ ታይፈስ አምጪ ዝርያዎች አሉት። ሶስት ዋና ዋና የታይፈስ አይነቶች አሉ፡፡

  ሙሪን (Murine typhus)፣

  ኢፒደሚክ ወይም ወረርሽኝ (Epidemie typhus)

  ስክረብ (Scrub typhus )ታይፈስ ናቸው

      በኢትዮጵያ የተለመደው የታይፈስ አይነት ኢፒደሚክ ታይፈስ ስለሆነ እሱን ነጥለን እናያለን።

የታይፈስ በሽታን እንዴት ይከሰታል ?

የታይፈስ በሽታ የሚከሰተው ታይፈስ አምጪ ተህዋሲኑን በተሸከሙ የቅማል ወይም የቁንጫ አይነምድር ሰዉነት ላይ ሲያርፍ እና፤ ከዚያም በምናሳካክበት ግዜ ወይም በሌላ ምክንያት በተፈጠረ የቆዳ ክፍተት ወደ ቆዳ ሲገባ ነው።

ታይፈስ ምን አይነት ምልክቶችን ያስከትላል ?

የታይፈስ በሽታ የያዘው ሰው የሚከተሉትን ምልክቶች ሊያሳይ ይችላል።

  ትኩሳት

 ብርድ ብርድ ማለት

  ማንቀጥቀጥ

  ራስ ምታት

  የጡንቻ ህመም እና አልፎ አልፎ ደግሞ ሽፍታ (rash) ዋና ዋና የታይፈስ ምልክቶች ናቸው፡፡

  ባስ ሲል በተለይ የኢፒደሚክ ታይፈስ ላይ የአእምሮ ብዥታ ፣ሳል፣ማቅለሽለሽ እና ማስታወክ ሊኖር ይችላል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *