ተቅማጥ

ተቅማጥ (Diarhea)

ተቅማጥ በአማርኛ በተለያዩ ቦታወች የተለያዩ ስያሜዎች አሉት። ለምሳሌ ቁልቁል ይባላል። ወደታች፣ ሸርተቴ፣ቅዘን ወዘተ ይገኙበታል።ተቅማጥ የራሱ ትርጓሜ አለው። ትርጓሜውን ስንመለከት፣በቀን ከሶስት ግዜ በላይ ሰገራ ከወጣን፣ ሰገራችን ቀጭን ከሆነ ወይም ሰገራችን በቀን ከ200 ግራም በላይ ከሆነ ነው።

 

 

ተቅማጥ ከቆይታ አንጻር በሶስት ከፍሎ ማየት ያስፈልጋል።

  • የመጀመሪያው ለአጭር ጊዜ (<14 ቀን) የሚቆይ ሲሆን አጣዳፊ ተቅማጥ ይባላል።
  • ሁለተኛው ከ4 እስከ 30 ቀናት የሚቆይ ነው፤ ይህም ፐርሲስተንት ተቅማጥ (persistent diarrhea) ይባላል።
  • ሶስተኛው የተቅማጥ አይነት ከ30 ቀናት በላይ ይቆያል፤ይህኛው ዘውታሪ ወይም ስር የሰደደ ተቅማጥ (chronic diarrhea) ይባላል።

መንስኤ እና አመጣጥ

በርካታ ሁኔታዎች እና በሽታዎች ተቅማጥ ያስከትላሉ።ተቅማጥ የሚከሰተው ከአንጀት ወደ ሰዉነት (ደም ስር) መዋሃድ ያለበት ዉሃ እና ንጥረ ነገር በአግባቡ ሳይወሃድ ሲቀር ወይም ከደም ስር (ከሰውነት) ወደ አንጀት ዉሃ እና ንጥረ ነገር ሲመነጭ ነው። ከምግብ አለመስማማት እስከ ኤች አይ ቪ ኤድስ ድረስ ያሉ ችግሮች ተቅማጥ ያስከትላሉ።

የተለያዩ መንስኤዎች የተለያየ የተቅማጥ ባህሪ አላቸው።

  • ለምሳሌ አሜባ አጣዳፊ ተቅማጥ ያስከትላል
  • ክሪፕቶስፖሪዲያ ዘውታሪ ተቅማጥ በማምጣት ይታወቃል።
  • የምግብ መመረዝ (food poisoning)
  • ባክቴሪያ(ሳልሞኔላ፣ሺጌላ፣ኢስቸርቺያ ወዘተ)
  • ፕሮቶዘዋ (አሜባ፣ጂያርዲያ፣ክሪፕቶስፖሪዲያ፣አይሶስፖራ ወዘተ)
  • ፓራሳይት (ስትሮንግሎይድ) ፣ቫይረስ (ሲኤም ቪ-CV፣ኤች አይ ቪ ኤድስ )
  • የአንጀት መቆጣት (አይ ቢ ኤስ-1BS፣ አይ ቢዲ-1BD) እና የአንጀት ካንሰር ተቅማጥን በማምጣት ይታወቃሉ፡፡

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *