ምግብ ውስጥ የሚገኙ ቁልፍ ንጥረ ነገሮች

ምግብ ውስጥ የሚገኙ ቁልፍ ንጥረ ነገሮች ምንድን ናቸው?
ቁልፍ ንጥረ ነገሮች ሰውነታችን ለመኖር፣ለማደግ እና ጤነኛ ለመሆን የሚያስፈልጉት የምግብ ንጥረ ነገሮች ናቸው።
ማክሮኒውትረንት(macronutrients) መጠናቸው የበዛ እና ማይክሮኒውትረንት(micronutrients) በትንሽ መጠን የሚፈለጉ
በመባል ለሁለት ይከፈላሉ።
1.
ካርቦሃይድሬትስ
ሚና ፦ ለሰውነታችን ዋነኛ የሀይል ምንጭ ነው
የሚገኝበት ምግብ፦ ሩዝ፣ዳቦ፣ፓስታ፣ድንች፣ፍራፍሬዎች፣አትክልቶች
2. ፕሮቲን
ሚና ፦ ቲሹዎችን() መገንባትና መጠገን፣እድገትን ማገዝ፣ኢንዛይም እና ሆርሞኖችን መስራት
የሚገኝበት ምግብ፦ ስጋ፣አሳ፣እንቁላል፣ባቄላ፣ምስር፣የወተት ተዋጽኦች፣ ለውዝ
3. ስብ(Fats)
ሚና ፦ ሀይል መስጠት ፣ቪታሚኖችን ወደ ሰውነት አካላት ለመሳብ(Vitamin A,D,E,K) የሰውነት አካላትን (Organs)
ለመጠበቅ
የሚገኝበት ምግብ፦ የወይራ ዘይት(olive oil)፣ለውዝ፣ዘሮች፣አሳ፣አቡካዶ(እነዚህ ጤናማ ስቦች ናቸው።)
4. ቫይታሚን
ሚና ፦ የሰውነትን ተግባራት ማገዝ እነዚህም የበሽታ መከላከል፣የአይን እይታ፣የአጥንት ጤና እና ከበሽታ ማገገም
ምሳሌዎች
 ቫይታሚን A (ዓይን፣ቆዳ፦ካሮት፣ስኳር ድንች
 ቫይታሚን C (በሽታ መከላከል፣ማገገም)፦ ብርቱካን ፣ቲማቲም
 ቫይታሚን D (አጥንት)፦ የጸሃይ ብርሀን፣አሳ፣እንቁላል
 ቫይታሚን K (ለደም መረጋጋት)፦ አረንጓዴ ቅጠሎች
5. ማዕድናቶች (Minerals)
ሚና፦ ጠንካራ አጥንቶችን ለመገንባት፣የልብ ጡንቻዎችን ለመቆጣጠር እና ለነርቮች
ምሳሊዎች
 ካልሲየም፦ወተት፣አይቤ፣አረንጓዴ ቅጠሎች(ለአጥንት እና ጥርስ)
 አይረን፦ስጋ፣ባቄላ፣ስፒናች(ለደም እና ሀይል)
 ፖታሺየም፦ሙዝ፣ድንች(ለጡንቻ እና ደም ግፊት)
6. ውሀ
ሚና፦ ለህይወት በጣም አስፈላጊ፣ለምግብ መፈጨት፣የምግብ ንጥረ ነገሮችን ለማጓጓዝ፣የሰውነት ሙቀትን ለመቆጣጠር፣
ቆሻሻን ከሰውነት ለማስወገድ ይረዳል።
የሚገኝበት፦ውሀን በመጠጣት፣ፍራፍሬዎችን (ሀብሀብ፣ብርቱካን)ሾርባ
በአጭሩ ካርቦሃይድሬቶች – ሀይል
ፕሮቲን- እድገት እና ጥገና
ስብ- ለአካላት ጤንነት ጥበቃ እና ሀይል
ቫይታሚ እና ማዕድናት – አካላትን ለመቆጣጠር/ለማስተካከል
ውሀ – ህይወትን ለማስቀጠል

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *